ቀጥታ፡

የኮሪደር ልማት ሥራዎች በፍጥነትና በጥራት እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2018 (ኢዜአ)፡- የኮሪደር ልማት ሥራዎች በፍጥነትና በጥራት እየተከናወኑ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ። 

ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በተገኙበት የኮሪደር ልማት ሥራዎች ግምገማ ተካሂዷል።

በዚሁ ወቅትም የተጀመሩ የኮሪደር ልማቶችን በተሻለ ፍጥነት ለማጠናቀቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ርዕሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል።


 

የኮሪደር ልማቱ በመደመር መንግሥት ዕሳቤ ፈጠራን፣ ፍጥነትና ጥራትን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለሕዝብ ክፍት ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ነው የገለጹት።

የኮሪደር ልማቱ የከተማውን ውብና ጽዱ ከማድረግ ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም ጠቁመዋል።

የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በሐረር ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ጭምር በማስፋት እየተከናወኑ ያሉ  ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልጸው፤ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በተለይም በጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያ እየተከናወነ ያለው አራተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ በፍጥነት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም