ቀጥታ፡

የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን በሁሉም መልክ ማልማት የሰርክ ተግባራችን ሊሆን ይገባል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 

አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2018(ኢዜአ)፦ የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን በሁሉም መልክ ማልማት የሰርክ ተግባራችን ሊሆን ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመለከቱ። 


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአካባቢ ጥበቃ ስርአታችን ደካማ በመሆኑ በድጋሚ ለመተካት እጅግ አስቸጋሪና ለም የሆነውን አፈራችንን  ስናጣ ቆይተናል ሲሉ ገልጸዋል። 



በህዝብና በመንግስት ትብብር የተጀመረው የአካባቢ ጥበቃ ሥራ የዝናብ ወራት ከመቃረቡ በፊት በዚህ መልክ መሰራት መጀመሩ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አመልክተዋል። 



ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፤ የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን በሁሉም መልክ ማልማት የሰርክ ተግባራችን ይሁን፤ እንበርታ፣ እጆቻችን አፈር ይንኩ፣ሀገር እናልማ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም