ማይክል ካሪክ የማንችስተር ዩናይትድ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማማ - ኢዜአ አማርኛ
ማይክል ካሪክ የማንችስተር ዩናይትድ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማማ
አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2018(ኢዜአ)፦ ማይክል ካሪክ ማንችስተር ዩናይትድን እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ በጊዜያዊነት ለማሰልጠን ከስምምነት ላይ ደርሷል።
የ44 ዓመቱ እንግሊዛዊ የአሰልጣኝነቱን ቦታ ያገኘው የቀድሞው የዩናይትድ አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ጋር ተወዳድሮ ካሸነፈ በኋላ መሆኑን የእንግሊዙ ጋዜጣ ዘ ሰን ይዞት በወጣው መረጃ ገልጿል።
ካሪክ ከዳረን ፍሌቸር ቦታውን በመረከብ ስራውን ነገ ጠዋት በይፋ ይጀምራል።
ማንችስተር ዩናይትድ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን ባለፈው ሳምንት ማሰናበቱ ይታወቃል።
የማንችስተር ዩናይትድ የቀድሞ ተጫዋች ካሪክ በ12 ዓመት የተጫዋችነት ቆይታው አምስት የፕሪሚየር ሊግ ጨምሮ 18 ዋንጫዎችን አንስቷል።
ካሪክ እ.አ.አ በ2021 የዩናይትድ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆኖ አገልግሎ ነበር።
ከእ.አ.አ 2022 እስከ 2025 የሚድልስቦሮው ዋና አሰልጣኝ በመሆን ሰርቷል።