ቀጥታ፡

በዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ሁለተኛ በመሆን ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑክ  አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2018(ኢዜአ)፦  በአሜሪካ ፍሎሪዳ በተካሄደው 46ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደርጎለታል። 

ልዑካን ቡድኑ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ፣  የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ  (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች  አቀባበል አድርገውታል ። 


 

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በሶስት የወርቅ፣ ሁለት የብር እና ሁለት የነሐስ በአጠቃላይ  ሰባት ሜዳሊያዎችን በማግኘት  ኬንያን ተከትላ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም