ቀጥታ፡

ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ የመጀመሪያ ዙር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይካሄዳሉ።

ምሽት አምስት ላይ ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ በሴይንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ።

በሩብ ፍጻሜው ኒውካስትል ዩናይትድ በሩብ ፍጻሜው ፉልሃምን፣ ማንችስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን አሸንፈዋል።

ኒውካስትል ዩናይትድ የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ነው።


 

ማንችስተር ሲቲ የካራባኦ ዋንጫን ስምንት ጊዜ በማንሳት ሊቨርፑል (10) ቀጥሎ ስኬታማው ክለብ ነው።

ቡድኖቹ እ.አ.አ በ2023 በውድድሩ ባደረጉት ብቸኛ ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ በኤሌክሳንደር ኢሳቅ ግብ 1 ለ 0 አሸንፏል። 

የሁለቱ ክለቦች የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም