ቀጥታ፡

ሊቨርፑል በኤፍኤ ካፕ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

አዲስ አበባ፤ ጥር 4 /2018 (ኢዜአ)፦ በኤፍኤ ካፕ የሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር ሊቨርፑል ባርንስሌይን 4 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም  በተደረገው ጨዋታ ዶሞኒክ ስቦዝላይ፣ ዠርሚ ፍሪምፖንግ፣ ፍሎሪያን ዊትዝ እና ሁጎ ኢኪቲኬ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

አዳም ፊሊፕስ ብቸኛውን ግብ ለባርንስሌይ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በጨዋታው ሊቨርፑል በኳስ ቁጥጥር ከፍተኛ ብልጫ ወስዷል። በግብ ሙከራዎችሞ የተሻለ ነበር።

ድሉን ተከትሎ ሊቨርፑል ወደ አራተኛ ዙር አልፏል። በቀጣዩ ዙር ከብራይተን ጋር ይጫወታሉ። ቀያዮቹ ስምንት ጊዜ ውድድሩን አሸንፈዋል።

የአንድ ጊዜ የዋንጫ ባለቤት ባርንስሌይ የኤፍኤ ካፕ ጉዞ ሶስተኛ ዙር ላይ ተገቷል። ቡድኑ በሊግ ዋን (በሶስተኛ ዲቪዚዮን) የሚጫወት ነው።

ከጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እየተካሄደ የሚገኘው የኤፍኤ ካፕ ሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር ነገ ይጠናቀቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም