ቀጥታ፡

ዣቪ አሎንሶ በገዛ ፍቃዱ ከሪያል ማድሪድ ጋር ተለያየ 

አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018(ኢዜአ) ሪያል ማድሪድ ከአሰልጣኙ ዣቪ አሎንሶ ጋር ተለያይቷል።

44 ዓመቱ ስፔናዊ በግንቦት ወር 2017 . በሶስት ዓመት ውል ነበር ለክለቡ የፈረመው።

ሪያል ማድሪድ ትናንት በስፔን አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ፍጻሜ በባርሴሎና መሸነፉ ከክለቡ ጋር ለመለያየቱ ምክንያት እንደሆነ ዓለም አቀፍ የስፖርት መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡት ይገኛል።

አሎንሶ በነጮቹ ቤት ለስድስት ወራት ከቆየ በኋላ በገዛ ፍቃዱ ከቡድኑ ጋር መለያየቱን ክለቡ አሳውቋል።

የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች አልቫሮ አርቤሎዋ የክለቡ አዲስ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾሟል።

42 ዓመቱ ስፔናዊ ከባለፈው ዓመት መጨረሻ አንስቶ የታዳጊ ቡድኑ (ካስቲያ) አሰልጣኝ ሆኖ ሲሰራ ቆይቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም