ቀጥታ፡

የአፋሕድ ምክትል ሊቀመንበር ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገቡ

አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018 (ኢዜአ)፦ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ምክትል ሊቀመንበር እና ወታደራዊ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ ከእነ ሙሉ ታጣቂዎቻቸው የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።

ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ አፋሕድ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር በአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ አማካኝነት ያደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሰላም ስምምነቱን በመቀበል ከነሙሉ ታጣቂዎቻቸው መግባታቸውን አሚኮ ዘግቧል።


 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአፋሕድ መካከል ሕዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም የዘላቂ ሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም