በኤፍኤ ካፕ ሊቨርፑል ከባርንስሌይ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
በኤፍኤ ካፕ ሊቨርፑል ከባርንስሌይ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር ሊቨርፑል ከባርንስሌይ ጋር ዛሬ ጨዋታውን ያደርጋል።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ከ45 ላይ በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ይካሄዳል።
ሊቨርፑል የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን ለስምንት ጊዜ በማንሳት ስኬታማ ከሚባሉ ክለቦች አንዱ ነው።
በእንግሊዝ ሶስተኛ የሊግ የውድድር እርከን (ሊግ ዋን) የሚገኘው ባርንስሌይ አንድ ጊዜ ውድድሩን አሸንፏል።
ሁለቱ ክለቦች በኤፍኤ ካፕ ሲገናኙ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።
እ.አ.አ 1985 ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝተው ሊቨርፑል 4 ለ 1 አሸንፏል።
እ.አ.አ በ2008 16 ውስጥ ባደረጉት ጨዋታ ባርንስሌይ ሊቨርፑልን ሳይጠበቅ 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ገብቷል።
ክለቦቹ ከ18 ዓመታት በኋላ በመድረኩ ይገናኛሉ።
ሊቨርፑል ጨዋታውን የማሸነፍ የቅድሚያ ግምት አግኝቷል።
የኤፍኤ ካፕ የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን ነገ ይጠናቀቃል።
155 ዓመታትን ያስቆጠረው ኤፍኤ ካፕ የዓለም አንጋፋው የክለቦች ውድድር ነው።