ናይጄሪያ ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች - ኢዜአ አማርኛ
ናይጄሪያ ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች
አዲስ አበባ፤ ጥር 2 /2018 (ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሶስተኛ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር ናይጄሪያ አልጄሪያን 2 ለ 0 አሸንፋለች።
ማምሻውን በማራካሽ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቪክቶር ኦሲሜን በ47ኛው እና አኮር አዳምስ በ57ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ኦሲሜን በውድድሩ ላይ ያስቆጠራቸውን ግቦች ብዛት ወደ አራት ከፍ በማድረግ በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ፉክክሩ አምስት ግቦች ያለውን የሞሮኮውን ብራሂም ዲያዝ ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በጨዋታው ላይ ናይጄሪያ በተጋጣሚዋ ላይ ከፍተኛ ብልጫ ወስዳለች። ንስሮቹ ተጨማሪ ግቦችን ለማስቆጠር የሚችሉባቸውን እድሎች አልተጠቀሙም።
ውጤቱን ተከትሎ ናይጄሪያ ግማሽ ፍጻሜ የገባች ሶስተኛ ሀገር ሆናለች። በግማሽ ፍጻሜው ከአዘጋጇ ሞሮኮ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ከወዲሁ ተጠባቂ ነው።
ምሽት አራት ሰዓት ላይ የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቯር ከግብጽ በአጋዲር ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።