ማንችስተር ሲቲ ኤክስተር ሲቲን 10 ለ 1 በማሸነፍ በኤፍኤ ካፕ ቀጣዩን ዙር ተቀላቀለ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ኤክስተር ሲቲን 10 ለ 1 በማሸነፍ በኤፍኤ ካፕ ቀጣዩን ዙር ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፤ ጥር 2 /2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ኤፍኤካፕ የሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ኤክስተር ሲቲን 10 ለ 1 ረቷል።
ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሮድሪ፣ ራያን ማይካዶ፣ ማክስ አሊይን፣ ሪኮ ሉዊስ፣ አንቶዋን ሴሜንዮ፣ ናታን አኬ፣ ቲጃኒ ራይንደርስ፣ ኒኮ ኦራይሊ እንዲሁም የኤክስተሮቹ ጃክ ፊትዝዋተር እና ጃክ ዶይል-ሄይስ በራሳቸው ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ጆርጅ ቢርች ለኤክስተር ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
ከቦርንማውዝ የፈረመው አንቶዋን ሴሜኒዮ የመጀመሪያ ጎሉን ለሲቲ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ ወደ አራተኛ ዙር አልፏል።