ኢትዮጵያ መድን ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ መድን ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ጥር 2 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድን ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በረከት ካሌብ እና ብሩክ ሙሉጌታ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ቴዎድሮስ ኃይለማርያም ለወላይታ ድቻን ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮጵያ መድን በ16 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 15ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ አራተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ በ12 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ጨዋታውን ተከትሎ የ14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።
የ5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳሉ።