ኢትዮጵያ በዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፤ ጥር 2 /2018 (ኢዜአ)፦ 46ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ማምሻውን በአሜሪካ ፍሎሪዳ እየተካሄደ ይገኛል።
ከ20 ዓመት በታች ሴቶች የስድስት ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ማርታ ዓለማየሁ በ18 ደቂቃ 52 ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ በሻምፒዮናው የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ወሰኔ አሰፋ 19 ደቂቃ ከ19 ሴኮንድ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።
የኔነሽ ሽመክት 19 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ አምስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።