ቀጥታ፡

መቀሌ 70 እንደርታ እና ሸገር ከተማ ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ፤ ጥር 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ እና ሸገር ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሄዷል።

መቀሌ 70 እንደርታ በ12 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።


 

ሸገር ከተማ በ14 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 15ኛ ከፍ አድርጓል።

ዛሬ በተደረጉ ሌሎች የ14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሃዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም