ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ አርሰናል ከሊቨርፑል አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል እና ሊቨርፑል ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል።

ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ አርሰናል በሁለተኛው አጋማሽ ሊቨርፑል ብልጫ ወስደው ተጫውተዋል።

አርሰናል በጨዋታው በአንጻራዊነት የግብ እድሎችን በተሻለ ሁኔታ ቢፈጥርም ለማሸነፍ በቂ አልነበሩም።

በጉዳት አጥቂዎቹን ያጣው ሊቨርፑል የማጥቃት እንቅስቃሴው ላይ ተጽእኖ አሳድሯል።

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል ነጥቡን ወደ 49 ከፍ ሲያደርግ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለው ልዩነት በነበረበት ስድስት ነጥብ ቀጥሏል።

ሊቨርፑል በ35 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

ሊቨርፑል አርሰናልን በሊጉ ሁለት ጨዋታዎች ግብ እንዳያስቆጥር ማድረግ ችሏል።

ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ሊቨርፑል 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም