የሊጉ መሪ ሲዳማ ነጥብ ጣለ - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ ሲዳማ ነጥብ ጣለ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሲዳማ ቡና እና አርባምንጭ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተደርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ከፍ አድርጓል። ከተከታዩ ነጌሌ አርሲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት ያገኘውን እድል አልተጠቀመም።
አርባምንጭ ከተማ በስምንት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል። በሊጉ እስከ አሁን ምንም ጨዋታ ያላሸነፈ ብቸኛ ቡድን ነው።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሃ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከአዳማ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ኪሩቤል ወንድሙ ለወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በጨዋታ እና ቢኒያም አይተን በፍጹም ቅጣት ለአዳማ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በ14ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ነጌሌ አርሲ ምድረ ገነት ሽሬን 1 ለ 0 አሸንፏል።