ቀጥታ፡

ባርሴሎና በስፔን የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ለፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 29/2018(ኢዜአ)፦  በስፔን የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና አትሌቲኮ ቢልባኦን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

ማምሻውን በሳዑዲ አረቢያ ኪንግ አብደላ ስፖርትስ ሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራፊኒያ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፌርሚን ሎፔዝ፣ ፌራን ቶሬስ እና ሮኒ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በጨዋታው ላይ ባርሴሎና ከፍተኛ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።

ባርሴሎና በስፔን የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ለፍጻሜ ያለፈ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።

በፍጻሜው ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ሪያል ማድሪድ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

አትሌቲኮ ማድሪድ እና ሪያል ማድሪድ ነገ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም