ቀጥታ፡

የገና በዓል በላሊበላ ከተማ በድምቀት እንዲከበር ላደረጉ ሁሉ ፖሊስ ምስጋና አቀረበ 

ወልዲያ፤ታኅሣስ 29/2018 (ኢዜአ)፦ በርካታ ታዳሚዎችና ምእመናን የተገኙበት የገና በዓል በላሊበላ ከተማ በተሳካ መልኩ እንዲከበር ላደረጉ ሁሉ የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ምስጋና አቀረበ። 

የገና በዓል በላሊበላ ከተማ በርካታ ምዕመናን፣ የውጭና የሀገር ውስጥ ታዳሚዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።


 

የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ፈንታ ተጋፋው፤ የአካባቢው ህብረተሰብ፣ ወጣቶችና የጸጥታ አካላት በዓሉ በተሳካ መልኩ እንዲከበር ሌት ከቀን ያደረጉትን ትጋትና ጠንካራ ትብብር አድንቀዋል።


 

ከሁሉም አካባቢዎች በርካታ ምእመናን እና ጎብኝዎች በተለያዩ የመጓጓዣ አማራጮችና በእግር ጭምር በመጓዝ ላሊበላ መገኘታቸውን በመግለጽ በዓሉ ከዋዜማው እስከ ፍፃሜው በተሳካ መልኩ ተከብሮ ተጠናቋል ብለዋል።


 

ለዚህም ፖሊስና ሌሎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም አጠቃላይ የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረጉት የላቀ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም