የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 29/2018 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል(ገና) መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የገና በዓል ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሰላም እና የደስታ እንዲሆን ተመኝቷል።
በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ገልጿል።
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን የገለጸው በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ ነው።
በኢትዮጵያ የዩነናይትድ ኪንግደም ኤምባሲ የገና በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የአንድነት እንዲሆን ተመኝቷል።
በኢትዮጵያ የጅቡቲ አምባሳደር እና በአፍሪካ ህብረት እና ኢሲኤ ቋሚ መልዕክተኛ አብዲ መሀሙድ ኢይቤ በኤክስ ገጻቸው፥ ባሰፈሩት መልዕክት ለመላው ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ እና እህቶቼ መልካም የገና በዓል እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።
በኢትዮጵያ የአርሜኒያ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ስዊዘርላንድ፣ ፓኪስታን ኤምባሲዎችም መልካም የገና በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል።
በተያያዘም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ የገና በዓል የሰላምና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይኦኤም) በበኩሉ፥ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን መልካም የገና በዓል ያለ ሲሆን በዓሉ ለእምነቱ ተከታዮች ደስታ እና ሰላም ይዞ እንዲመጣ ተመኝቷል።
የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) የገና በዓል የደስታ እና የበረከት እንዲሆን ተመኝቷል።
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው።