ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ከብራይተን ይጫወታል 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 29/2018 (ኢዜአ)፦  በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። 

ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ሲቲ ከብራይተን በኢትሃድ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል። 

ማንችስተር ሲቲ በ42 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ብራይተን በ28 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ነጥብ የጣለው ማንችስተር ሲቲ ማሸነፍ ከአርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ ሶስት ዝቅ ማድረግ ያስችለዋል።

ብራይተን ካሸነፈ በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘግባል። 

በሌሎች መርሃ ግብሮች በርንሌይ ከማንችስተር ዩናይትድ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን ያሰናበተው ማንችስተር ዩናይትድ በጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳረን ፍሌቸር እየተመራ ወደ ሜዳ ይገባል።

በርንሌይ ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። 

ክሪስታል ፓላስ ከአስቶንቪላ፣ ፉልሃም ከቼልሲ፣ ብሬንትፎርድ ከሰንደርላንድ፣ ቦርንማውዝ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ኤቨርተን ከዎልቭስ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ይጫወታሉ። 

ኒውካስትል ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም