ኖቲንግሃም ፎረስት ዌስትሃም ዩናይትድን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
ኖቲንግሃም ፎረስት ዌስትሃም ዩናይትድን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኖቲንግሃም ፎረስት ዌስትሃም ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በለንደን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የኖቲንግሃም ፎረስት ተከላካይ ሙሪሎ በ13ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ያስቆጠረው ጎል ዌስትሃምን መሪ አድርጓል።
ኒኮላስ ዶሚኒጌዝ በ55ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፈው ጎል ኖቲንግሃም ፎረስት አቻ ሆኗል።
ሞርጋን ጊብስ-ዋይት በ89ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረው ግብ ለፎረስት ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስገኝቷል።
የዌስትሃም ዩናይትዱ ክሪሴንሲዮ ሳመርቪል በ51ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት (ቫር) ታይቶ ከጨዋታ ውጪ በመሆኑ ምክንያት ሊሻር ችሏል።
ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኖቲንግሃም ፎረስት በ21 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል። በሊጉ ስድስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በውድድር ዓመቱ 13ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ዌስትሃም ዩናይትድ በ14 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሌ።
ዌስትሃም ዩናይትድ ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።