ቀጥታ፡

አልጄሪያ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሰባተኛ የጥሎ ማለፍ መርሃ ግብር አልጄሪያ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ማምሻውን በፕሪንስ ሙላይ ኤል ሀሰን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በ90 ደቂቃ  ምንም ግብ ባለመቆጠሩ ምክንያት 30 ደቂቃ ተጨምሯል።

በተጨማሪ ሰዓት አዲል ቡልቢና በ119ኛው ደቂቃ አልጄሪያን አሸናፊ ያደረገችውን ወሳኝ ግብ አስቆጥሯል።

አልጄሪያ ሩብ ፍጻሜ የገባች ሰባተኛ ሀገር ሆናለች።

በሩብ ፍጻሜው ከናይጄሪያ ጋር የምትጫወት ይሆናል።

የጥሎ ማለፍ የመጨረሻ ጨዋታ በወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቯር እና ቡርኪናፋሶ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በማራካሽ ስታዲየም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም