ሊያም ሮሴንየር የቼልሲ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
ሊያም ሮሴንየር የቼልሲ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ቼልሲ ሊያም ሮሴንየርን የክለቡ ዋና አሰልጣኝኝ አድርጉ ዛሬ በይፋ መሾሙን አስታወቀ።
ሮሴንየር ከምዕራብ ለንደኑ ክለብ ጋር እስከ እ.አ.አ 2032 የሚያቆያቸውን ውል ተፈራርመዋል።
የ41 ዓመቱ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ላለፉት ሁለት ዓመታት በፈረንሳዩ ስትራስቡርግ ክለብ ሲያሰለጥኑ ቆይተዋል።
ቼልሲ ባለፈው ሳምንት ጣልያናዊውን አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካን ማሰናበቱ የሚታወስ ነው።