ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ሰራተኞች የገና በዓልን በማስመልከት ማዕድ አጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ሰራተኞች የገና በዓልን በማስመልከት ማዕድ አጋሩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ሰራተኞች የገና በዓልን በማስመልከት ማዕድ አጋርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በማህበራዊ ትስሰር ገጹ ባወጣው መረጃ አመራርነት በፖሊሲ እና በተቋማት ብቻ ሳይሆን በሰብአዊ ግንኙነቶችም ጭምር ይከናወናል ሲል ገልጿል።
ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የገና በዓልን ለማክበር በሚሰናዱበት እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከሚገኙ ሠራተኞች መሀል መገኘታቸውን አመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁልጊዜም በበዓላት ጊዜ እንደሚያደርጉት አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞች እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤቱ ለሚደግፋቸውና ለሚያሳድጋቸው ሕፃናት የበዓል ስጦታዎችን መስጠታቸውንና ማዕድ ማጋራታቸውን አስታውቋል።
ይኽም በየዕለቱ አስተዋጽኦዋቸው ጎልቶ ባይነገርም ለሀገር የሚያገልግሉ ሠራተኞችን እውቅና የሠጠ፣ ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትም በማኅበረሰባችን ስፍራ እንዳላቸው የሚያሳይ ፍቅርን ያካፈለ ተግባር ነው ሲል ነው ጽህፈት ቤቱ ያመለከተው።