ቀጥታ፡

ናይጄሪያ ለሩብ ፍጻሜ አለፈች

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሃ ግብር ናይጄሪያ ሞዛምቢክን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች።

ማምሻውን በፌዝ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቪክቶር ኦሲሜን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አዴሞላ ሉክማን እና አኮር አዳምስ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በጨዋታው ላይ ናይጄሪያ ከፍተኛ ብልጫ የወሰደች ሲሆን ተመጣጣኝ ፉክክር ለማየት አልታቸለም።

የናይጄሪያው የክንፍ መስመር ተጫዋች አዴሞላ ሉክማን የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።

ውጤቱን ተከትሎ ናይጄሪያ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለች ስድስተኛ ሀገር ሆናለች።

በሩብ ፍጻሜው ከአልጄሪያ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም