ግብጽ ለሩብ ፍጻሜ አለፈች - ኢዜአ አማርኛ
ግብጽ ለሩብ ፍጻሜ አለፈች
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አምስተኛ የጥሎ ማለፍ መርሃ ግብር ግብጽ ቤኒንን 3 ለ 1 አሸንፋለች።
ማምሻውን በአጋዲር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሐመድ አቴያ በ69ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ግብጽን መሪ አድርጋለች።
ጆዴል ዶሱ በ83ኛው ደቂቃ የቤኒን የአቻነት ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርቷል።
በጭማሪው ሰዓት ያስር ኢብራሂም በ97ኛው እና መሐመድ ሳላህ በ124ኛው ደቂቃ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ግብጽን አሸናፊ አድርጓል።
ቡድኖቹ በጨዋታው ላይ ጠንካራ ፉክክር አድርገዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ሩብ ፍጻሜ የገባች አምስተኛ ሀገር ትሆናለች። በሩብ ፍጻሜው ከኮትዲቯር እና ቡርኪናፋሶ ትጫወታለች።