መቀሌ 70 እንደርታ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
መቀሌ 70 እንደርታ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍጹም ዓለሙ በ25ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው መቀሌ 70 እንደርታ በ11 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በአንጻሩ በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ መድን በ13 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።
የ14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።