የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የካቲት 7 ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የካቲት 7 ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ወንዶች ከፍተኛ ሊግ የሁለተኛ ዙር ውድድር ከየካቲት 22 ጀምሮ የምድብ ሀ በጅማ፣ የምድብ ለ በሃዋሳ እንደሚካሄዱ ገልጿል።
የዝውውር ጊዜው ደግሞ ከጥር 20 እስከ የካቲት 17 ክፍት ሆኖ ይቆያል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የሁለተኛ ዙር ውድድር ከየካቲት 28 ጀምሮ በሰበታ ከተማ እንደሚካሄድ ያስታወቀው ፌዴሬሽኑ የዝውውር ጊዜ ደግሞ ከጥር 28 እስከ የካቲት 25 ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ነው ያመለከተው።
የኢትዮጵያ ሊግ አንድ ሁለተኛ ዙር ውድድር ከየካቲት 14 ጀምሮ እንደሚደርግ እና የውድድር ቦታ ወደፊት እንደሚገለጽ ታውቋል።