አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በሁለት ዓመት ውል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በሁለት ዓመት ውል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 27/2018 (ኢዜአ)፦ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በሁለት ዓመታት የውል ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ዛሬ በይፋ መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በመምረጥ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።
አሰልጣኝ ዮሐንስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ የነበሩ ሲሆን ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ታዳጊ እና ዋናው ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት ከመምራታቸው በተጨማሪ ፌዴሬሽኑን በቴክኒክ ዳይሬክተርነት አገልግለዋል።