ቀጥታ፡

በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ተሰማርተን ከተረጂነት ወጥተናል - ተጠቃሚዎች

ሐረር፤ ታህሳስ 27/2018(ኢዜአ)፦ በከተማ  ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ተሰማርተው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገራቸውን በሐረር ከተማ በፕሮግራሙ ታቅፈው ለምረቃ የበቁ ተጠቃሚዎች ተናገሩ።

በሐረር ከተማ በልማታዊ ሴፍቲኔት ታቅፈው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የተሸጋገሩ እማወራና አባወራዎች ዛሬ  ተመርቀዋል።


 

ወይዘሮ ዘመድ አገኘው በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም መታቀፋቸው የሥራ ባህላቸውን በመለወጥ ባከናወኑት የምግብ ቤት ስራ ከድህነት መውጣት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ታቅፈው በልማትና በሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ በመሰማራታቸው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገራቸውን የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ጫልቱ ኢብራሂም ናቸው።

ወይዘሮ መፍቱሃ ሃይሌም በፕሮግራሙ ለሶስት ዓመታት በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች በመሰማራት እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከመርዳት ባለፈ ከሚያገኙት በመቆጠብ የተሻለ ጥሪት ማፍራት መቻላቸውን ገልጸዋል።

ወይዘሮ መቅደስ ባህሩ በበኩላቸው በፕሮግራሙ ታቅፈው በሚደረግላቸው ድጋፍና በሚሰሩት ስራ ጠንክረው በመስራት  ተጠቃሚ መሆናቸውንና ለሌሎችም ተሞክሯቸውን እንደሚያካፍሉ ተናግረዋል።


 

የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፈርሃን ዚያድ እንዳሉት በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም  በቀጥታ ድጋፍ እና በአካባቢ ልማት ስራ 3ሺህ 695 ዜጎች ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።

በዛሬው እለትም በፕሮግራሙ ለሶስት ዓመታት ታቅፈው የተሰጣቸውን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየርና ጠንክረው በመስራት እራሳቸውን ከመቻል ባለፈ ለሌሎች የስራ እድል መፍጠራቸውን ተናግረዋል።

ሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ ያህያ አብዱረሂ እንዳሉት የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ያበቃቸውን ተሞክሮ ለሌሎች ማካፈል አለባቸው

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም