የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን ማጎልበት ይገባል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን ማጎልበት ይገባል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በራስ አቅም እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን ማጎልበት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡና በተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሂደዋል።
በዓሉ ፍቅርና መተሳሰብ የሚገለጥበት መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባዋ፥ ከተማ አስተዳደሩ ዛሬ ያበረከተው የበዓል ስጦታ ለነዋሪዎች ያለውን ፍቅር በተግባር ያሳየበት መሆኑን ተናግረዋል።
በከተማ ደረጃ ከ300 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖች የማዕድ የማጋራት ተግባር መከናወኑን ጠቁመዋል፡፡
በመዲናዋ የመረዳዳትና የአብሮነት እሴት ይበልጥ እንዲጸና እያደረጉ ላሉ በጎ አድራጊ ባለሀብቶችና ወጣቶች በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ጊዜያዊ ችግሮችን ለማለፍ በራስ አቅም እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን ማጎልበት እንደሚገባም ገልጸዋል።