ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ሽረ ምድረ ገነት ኢትዮጵያ ቡናን አሸንፏል

አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 26/2018 (ኢዜአ)፡- በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሣምንት ጨዋታ ሽረ ምድረ ገነት ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 1 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲም በተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ፤ ዳንኤል ዳርጌ እና ሽመክት ጉግሳ (2) ባስቆጠሯቸው ግቦች ሽረ ምድረ ገነት ተጋጣሚውን ረትቷል።

በአንጻሩ የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ ግብ አቡበከር አዳሙ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

እንዲሁም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደረጉት ሸገር ከተማ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ግቦቹንም ዳዊት ካሳው በጨዋታ ለሸገር ከተማ እንዲሁም አዲስ ግደይ በፍጹም ቅጣት ምት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመረብ አሳርፈዋል።

ቀደም ብሎ 7 ሠዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የ13ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ጨዋታ በዳዊት ተፈራ እና አለኝታ ማርቆስ ግቦች ነጌሌ አርሲ መቻልን 2 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም