ቀጥታ፡

ነጌሌ አርሲ መቻልን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 26/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ነጌሌ አርሲ መቻልን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳዊት ተፈራ በ11ኛው እና አለኝታ ማርቆስ በ31ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ነጌሌ አርሲ በ22 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል በ20 ነጥብ ከነበረበት ስድስተኛ ደረጃ ወደ ሰባተኛ ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም