ቀጥታ፡

አርሰናል ቦርንማውዝን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 25/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ቦርንማውዝን 3 ለ 2 አሸንፏል።

ማምሻውን በቫይታሊቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዴክላን ራይስ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጋብርኤል ማጋሌሽ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ኢቫኒልሰን እና ጁኒየር ክሩፒ ለቦርንማውዝ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ለኢቫኒልሰን ጎል መቆጠር ትልቅ ስህተት ሰርቶ የነበረው የአርሰናሉ ተከላካይ ጋብርኤል ማጋሌሽ ለመድፈኞቹ ግብ በማስቆጠር ቡድኑን ክሷል።

አርሰናል በሁለተኛው አጋማሽ የወሰደው ብልጫ ጨዋታውን እንዲያሸንፍ አስችሎታል።

በውድድር ዓመቱ 15ኛ ድሉን ያስመዘገበው የሊጉ መሪ አርሰናል ነጥቡን ወደ 48 ከፍ አድርጓል።

ከተከታዩ አስቶንቪላ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ከፍ ማድረግ ችሏል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦርንማውዝ በ23 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ቡድኑ የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት 11 የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም