ሴኔጋል ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪዋ ሀገር ሆነች - ኢዜአ አማርኛ
ሴኔጋል ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪዋ ሀገር ሆነች
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሴኔጋል ሱዳንን 3 ለ 1 አሸንፋለች።
ማምሻውን በታንጀር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አሚር አብደላህ በስድስተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ሱዳን ሳትጠበቅ መሪ መሆን ችላ ነበር።
ይሁንና ፓፓ ጌይ በ29ኛው ደቂቃ እና በመጀመሪያው አጋማሽ የባከነ ሰዓት ጭማሪ እንዲሁም ተቀይሮ የገባው ታዳጊው ኢብራሂም እምባይ በ77ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በጨዋታው ላይ ሴኔጋል በሱዳን ላይ ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች።
ድሉን ተከትሎ ሴኔጋል ሩብ ፍጻሜ የገባች የመጀመሪያ ሀገር ሆናለች። በሩብ ፍጻሜው ከማሊ እና ታንዛንያ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።
ማሊ እና ቱኒዚያ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በመሐመድ አምስተኛ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።