አርባምንጭ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አርባምንጭ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርባምንጭ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተከናውኗል።
ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ በሰባት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።
አርባምንጭ ከተማ በሊጉ እስከ አሁን ምንም ጨዋታ ያላሸነፈ ብቸኛው ክለብ ነው።
ሃዋሳ ከተማ በ21 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ በተደረጉ የ13ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ድቻ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል።
አዳማ ከተማ ከፋሲል ከነማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።