ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮ ኤሌትሪክ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ21 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ10 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም