ኢትዮ-ቴሌኮም የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማቶችን ለባለ ዕድለኛ አሸናፊዎች አስረከበ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ-ቴሌኮም የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማቶችን ለባለ ዕድለኛ አሸናፊዎች አስረከበ
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 25/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮ-ቴሌኮም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መኪና ሽልማቶችን ለባለ ዕድለኛ አሸናፊ ደንበኞቹ አበርክቷል።
ኢትዮ ቴሌኮም 130ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን በማስመልከት ያዘጋጀውን ሁለት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማቶች ለአሸናፊ ደንበኞቹ አስረክቧል፡፡
ኩባንያው በሽልማት መርሃ-ግብሩ ላይ ተጨማሪ ስድስት ዘመናዊ መኪኖችን የሽልማት ዕጣዎችን የማውጣት ሥነ-ሥርዓት አከናውኗል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ የሽልማት መርሃ-ግብር ከዚህ ቀደም አራት የኤሌክትሪክ መኪኖችን እንዲሁም 13 ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን ለባለ ዕድለኛ ደንበኞቹ ማስረከቡን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም 372 ዘመናዊ ስማርት ስልኮችንና የቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብን ጨምሮ በሽልማት መርሐ ግብሩ ከ127 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ አጠቃላይ ዋጋ ያላቸውን ሽልማቶች ሰጥቷል።
ኩባንያው በቀጣይም ደንበኞቹን ተሸላሚ የሚያደርገውን ቴሌ ፕለይ የተሰኘ የሽልማት መርሐ ግብሩን እንደሚያስቀጥልም ተገልጿል።
በዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮ-ቴሌኮም ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች፣ የሚዲያ አጋሮቻችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።