አስቶንቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
አስቶንቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ አስቶንቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆን ማክጊን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኦሊ ዋትኪንስ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ 13ኛ ድሉን ያስመዘገበው አስቶንቪላ በ42 ነጥብ ከሶስተኛ ደረጃ ወደ ሁለተኛ ከፍ ብሏል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኖቲንግሃም ፎረስት በ18 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል።
ሞርጋን ጊብስ-ዋይት ለኖቲንግሃም ፎረስት ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።