ቀጥታ፡

ወላይታ ድቻ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያዩ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል። 

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቴዎድሮስ ኃይለማርያም በ40ኛ ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ወላይታ ድቻ መሪ መሆን ችሎ ነበር።

ይሁንና ከእረፍት መልስ አቤል ያለው በ67ኛው ደቂቃ  ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ለቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ነጥብ አስገኝታለች።

ወላይታ ድቻ በ12 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በ19 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። ክለቡ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም