አዳማ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
አዳማ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ አዳማ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል።
አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።
ፋሲል ከነማ በ25 ነጥብ ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር በነጥብ እኩል ቢሆንም በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ፋሲል ከነማ በሊጉ ሽንፈት ያላስተናገደ ብቸኛው ቡድን ነው።