የሊጉ መሪ አርሰናል ከቦርንማውዝ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ አርሰናል ከቦርንማውዝ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 25/2018 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ይጀመራል።
በዕለቱ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ በቫይታሊቲ ስታዲየም ቦርንማውዝ ከአርሰናል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ቦርንማውዝ በ23 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል።አርሰናል በ45 ነጥብ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል።
ባለሜዳው ቦርንማውዝ ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም። ተጋጣሚው አርሰናል ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች አሸንፏል።
ጨዋታው ቦርንማውዝ ከሁለት ወር በላይ የዘለቀ ያለማሸነፍ ጉዞውን ለመቀልበስ፣ አርሰናል መሪነቱን ለማጠናከር የሚያደርጉት ነው ።
አርሰናል ካሸነፈ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ከፍ ያደርጋል።
በሌሎች መርሃ ግብሮች በሊጉ ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አስቶንቪላ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
ብራይተን ከበርንሌይ እና ዎልቭስ ከዌስትሃም ዩናይትድ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።