ኢትዮጵያ የቦንድ እዳ ሽግሽግ በተመለከተ ከዓለም አቀፍ የቦንድ ባለቤቶች ጋር የመነሻ ስምምነት ላይ ደረሰች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የቦንድ እዳ ሽግሽግ በተመለከተ ከዓለም አቀፍ የቦንድ ባለቤቶች ጋር የመነሻ ስምምነት ላይ ደረሰች
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 24/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአንድ ቢሊዮን ዶላር የቦንድ እዳ ሽግሽግን በተመለከተ ከዓለም አቀፍ የቦንድ ባለቤቶች ጋር የመነሻ ስምምነት ላይ መድረሷን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የመነሻ ስምምነት ላይ የተደረሰው ከታህሳስ 14 እስከ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በቦንዱ ላይ ከ45 በመቶ በላይ ካላቸው ባለሀብቶች ከተደረገው ድርድር በኋላ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
ስምምነቱ የኢትዮጵያ የእዳ ጫናን የሚያቃልሉ መሰረታዊ የፋይናንስ ሁኔታዎችን በግልጽ ማስቀመጡን በመግለጫው ላይ ተመላክቷል።
እዳውን የማቃለል እቅዱ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና ዓለም አቀፍ የእዳ ህጎችን የተከተለ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ እቅዱን አይኤምኤፍ እና ኦፊሴላዊ አበዳሪዎች እንዲያፀድቁት መቅረቡን ጠቁሟል።
ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2026 ቀሪ ጉዳዮችን ለማጠናቀቅ እና የቦንድ ማዋቀር ስራውን ለመጨረስ እንደምትሰራ ተመላክቷል።
#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ