ቀጥታ፡

ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መሳካት ዘመኑን የዋጁ የሥልጠና ፕሮግራሞች እየተከፈቱ ነው

አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 24/2018 (ኢዜአ)- ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መሳካት በዘርፉ ብቁ ባለሙያ ለማፍራት ዘመኑን የዋጁ የሥልጠና ፕሮግራሞች እየተከፈቱ መሆኑ ተገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ባስጀመሩበት ወቅት፤ ስትራቴጂው ተደራሽ፣ ፍትሐዊ እና አስተማማኝ የዲጂታል ምኅዳር መፍጠር ላይ ማተኮሩን ገልጸዋል።


 

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (/) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በቴክኒክና ሙያ መስክ አበረታች ለውጥ እንዲመዘገብ ዐቅም ፈጥሯል።

ለአብነትም ስትራቴጂው ኢንስቲትዩቱ የአሰለጣጠን ሂደቱን ዘመኑን በዋጀ መልኩ እንዲቃኝና የሰዎችን የዲጂታላይዜሽን ግንዛቤ እንዲጎለብት መሰረት መጣሉን አንስተዋል።

ኢንስቲትዩቱ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሊያሳካቸው ከያዛቸው ዓላማዎች ጋር በማስተሳሰር ለመተግበር የሚያስችለውን የሠነድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂክ ግቦችን ለማሳካት የተሻለ የዲጂታል ክኅሎት ያላቸው ሰልጣኞችን ማፍራት በትኩረት የሚሠራበት ጉዳይ መሆኑን አመላክተዋል።

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የሳይበር ሴክዩሪቲና ሌሎች የሥልጠና ዓይነቶች ለስትራቴጂው መሳካት ሚናቸው የላቀ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል።

በተጨማሪም በዲጂታል ክኅሎት የበለጸገ ባለሙያ ለማፍራትና የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በተሻለ መንገድ ለማበልጸግ ተቋሙ ራሱን በግብዓትና በአደረጃጀት እያጠናከረ እንደሚገኝም ነው ያስታወቁት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም