ቀጥታ፡

ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የመስኅብ ሥፍራዎች እየለሙ ነው

አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 24/2018(ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም የሚረዱ የመዳረሻ ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ።

የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይኒቱ መልኩ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የጎብኚ የቆይታ ጊዜን ለማራዘም በመዳረሻዎች አካባቢ ከዚህ ቀደም ለጎብኚ ምቹ ያልነበሩ ቦታዎችን የማልማትና ተጨማሪ አገልግሎቶችን የማስፋፋት ሥራ እየተከናወነ ነው።

ለዚህም እስካሁን ከ1 ቢሊየን 200 ሚሊየን በላይ ወጪ የሚጠይቁ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡


 

በያዝነው የበጀት ዓመት እየለሙ ከሚገኙት አምስት መዳረሻዎች መካከልም አራቱ አዲስ ቀሪው ነባርና በአዲስ መልክ የሚለማ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም በሁሉም ዞኖች የሚገኙ መስኅቦችን በማልማት ለጎብኚዎች ተደራሽ ለማድረግ የንቅናቄ ሥራ መከናወኑን ጠቅሰዋል።

በዚህ አግባብ በየዞኖቹ የሚገኙ መስኅቦችን በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ ሊለሙ የሚችሉ ተብለው መለየታቸውን ጠቁመዋል።


 

ከሀብት አንጻርም ባሉበት ደረጃ አሁን ባለው ዝግጅት በቅድሚያ ሊለሙ የሚችሉ እና መሠረተ-ልማት የሚፈልጉ በሚል በልየታው መታየቱን ነው ያስረዱት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም