አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 23/2018 (ኢዜአ)፦ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በመምረጥ ውሳኔ ማሳለፉን አመልክቷል።
አሰልጣኝ ዮሐንስ በአሁኑ ወቅት የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ታዳጊ እና ዋናው ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት ከመምራታቸው በተጨማሪ ፌዴሬሽኑን በቴክኒክ ዳይሬክተርነት ማገልገላቸው ተመላክቷል።
ፌዴሬሽኑ አሰልጣኙ እየሰሩበት ከሚገኘው ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር ንግግር ካደረገ በኋላ የውል ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።