ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ጣለ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 23/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሰንደርላንድ እና ማንችስተር ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ማምሻውን በስታዲየም ኦፍ ላይት በተካሄደው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድሎችን በመፍጠር የተሻለ የነበረ ቢሆንም ሊጠቀምባቸው አልቻለም።

ሰንደርላንድ በተደራጀ መከላከል እና የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ተጋጣሚውን ፈትኗል።


 

ውጤቱን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ነጥቡን ወደ 41 ከፍ አድርጓል።

ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ከፍ ብሏል።

ሰንደርላንድ በበኩሉ በ29 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ተቀምጧል።

ማምሻውን በተመሳሳይ ሰዓት በተደገ ሌላኛው ጨዋታ ብሬንትፎርድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ያለ ግብ አቻ ወጥተዋል።

ዛሬ አስቀድመው በተካሄዱ ጨዋታዎች ሊቨርፑል ከሊድስ ዩናይትድ ያለ ግብ አቻ ሲለያዩ የክሪስታል ፓላስ እና ፉልሃም ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ዛሬ በፈረንጆች 2026 አዲስ ዓመት የተደረጉት አራቱም የሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።

ጨዋታዎቹም የግብ ድርቀት አጋጥሟቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም