ሊቨርፑል እና ሊድስ ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል እና ሊድስ ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 23/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሊቨርፑል እና ሊድስ ዩናይትድ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሊቨርፑል የተሻለ የኳስ ቁጥጥር የነበረው ቢሆንም በቂ የግብ እድሎችን መፍጠር አልቻለም።
ሊድስ ዩናይትድ መከላከል እና መልሶ ማጥቃት የአጨዋወት ስልትን በመጠቀም አንድ ነጥብ ወስዷል።
ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በ33 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ሲይዝ ሊድስ ዩናይትድ በ21 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላኛው የምሽት ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ እና ፉልሃም አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ጂን-ፍሊፕ ማቴታ ለክሪስታል ፓላስ፣ ቶም ኬርኒ ለፉልሃም ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሌሎች የ19ኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች ምሽት 5 ሰዓት ሰንደርላንድ ከማንችስተር ሲቲ እና ብሬንትፎርድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ይጫወታሉ።