አግማስ ኢትዮጵያ በደብረብርሃን ለተቸገሩ ወገኖች የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
አግማስ ኢትዮጵያ በደብረብርሃን ለተቸገሩ ወገኖች የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረገ
ደብረብርሃን፤ ታህሳስ 23/ 2018 (ኢዜአ)፡- አግማስ ኢትዮጵያ በደብረብርሃን ለተቸገሩ ወገኖች 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረገ።
የተደረገው ድጋፍ የምግብ ዘይት፣ ዱቄት፣ አልባሳትና ሌሎችም አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ያካተተ ሲሆን የአግማስ ተወካዮች በስፍራው በመገኘት ድጋፉን አስረክበዋል።
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሰሜን ሸዋ ዞን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበባው መሰለ፤ በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር ለተዳረጉ ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬው እለት የአግማስ ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ያደረገው ድጋፍም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን አንስተው ለተደረገው እገዛ አመስግነዋል።
የአግማስ ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት የፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ኢሳ መሐመድ፤ በደብረብርሃን ከተማ ጊዜያዊ መጠለያ በመገኘት ድጋፉን አስረክበዋል።
የተደረገው ድጋፍም የምግብ ዘይት፣ ዱቄት፣ አልባሳትና ሌሎችም አስፈላጊ ቁሳቁሶች መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይነትም በመልሶ ማቋቋም ላይ ያተኮረ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።
የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑ ወገኖችም አግማስ ኢትዮጵያ በስፍራው በመገኘት ላደረገላቸው እገዛ አመስግነዋል።