ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 23/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ዛሬ በስልክ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር የአዲስ ዓመት መልዕክት መለዋወጣቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቅሰው፥ በውይይቱ በአሁናዊ እና ቀጣይ የሀገራቱ የሁለትዮሽ ትብብር ላይ መምከራቸውን ተናግረዋል።

የሁለቱ ሀገራት የጋራ ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦችን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመለዋወጥ ከስምምነት ላይ መደረሱንም አመልክተዋል።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም